No edit permissions for Amharic

መቅድመ ማንትራ

ኦም ፑርናም አዳሀ ፑርናም ኢዳም
ፑርናት ፑርናም ኡዳችያቴ
ፑርናስያ ፑርናም አዳያ
ፑርናም ኤቫ ቫሺሽያቴ

ኦም — ሁለንተናው የተሟላ፣ ፑርናም — ፍጹም ሙሉ የሆነ፣ አዳሀ — ያንኛው፣ ፑርናም — ፍጹም ሙሉ የሆነ፣ ኢዳም — ይህ የተከሰተው ዓለም፣ ፑርናት — ሁለንተናው ከተሟላው፣ ፑርናም — ፍጹም ሙሉ የሆነ፣ ኡዳችያቴ — የተፈጠረው፣ ፑርናስያ — ሁለንተናው ከተሟላው፣ ፑርናም — ባጠቃላይ ሙሉ በሙሉ፣ አዳያ — ምንም እንኳን የተወሰደ ቢሆንም፣ ፑርናም — በመመጣጠን ሁለንተናው ተሟልቶ የሚገኝ፣ ኤቫ — ምንም እንኳን፣ አቫሺሽያቴ — ቀሪ ሆኖ የሚኖር

ዓብዩ ጌታ ፍጹም እንከን የሌለው እና በሁሉም ረገድ ሁለንተናው የተሟላ ሆኖ የሚገኝ ነው፡፡ ፍጹም የተሟላ እና ፍጹም እንከን የሌለው በመሆኑም፣ በዚህ ቁሳዊ ዓለም ላይ በእርሱ የተፈጠሩ ሁሉ፣ ከእርሱ የሚመነጩ ፍጥረታት እንደመሆናቸው፣ ሁለንተናቸው የተሟላ ሆነው የተቀነባበሩ እና እንከን የለሽ ሆነው የተፈጠሩ ናቸው፡፡ ፍጹም ሙሉእ ከሆነው ከዓብዩ ጌታ የተፈጠሩ ሁሉ፣ በሁሉም ረገድ የተሟሉ ሆነው ተፈጥረዋል። ዓብዩ ጌታ ፍጹም የተሟላ አካል የያዘ በመሆኑም፣ ምንም እንኳን ብዙ የተሟሉ አካላት ከእርሱ የሚፈጠሩ ቢሆኑም፣ እርሱ ለዘለዓለም ሳይጎድል፣ ሁለንተናው የተሟላ ሆኖ ይኖራል፡፡” (ሽሪ ኡፓኒሻድ መቅድመ ማንትራ)

በዚህ ጥቅስ እንደተጠቀሰው ሁለንተናው የተሟላው እና ፍጹም እውነት የሆነው ዓብዩ ጌታ አምላካችን፣ የዓብዩ የመንግሥተ-ሰማያት ጌታ ነው፡፡ በሰብአዊነት ያልተከሰተውን የዓብዩ ጌታን መንፈስ ወይም “ብራህማን” መረዳት ወይም ደግሞ በልባችን ውስጥ የሚገኘውን “ፓራምአትማ” ተብሎ የሚታወቀውን የጌታ መንፈስ ማወቅ፤ ሁለንተናው የተሟላውን የዓብዩ ጌታን ሙሉ መንፈሳዊ አካል በትክክል ለማወቅ የሚያበቃን አይደለም። ዓብዩ የመንግሥተ-ሰማያት ጌታ “ሳት ቺት አናንዳ ቪግራሀ” ተብሎ ይታወቃል፡፡ በሰብአዊነት ያልተከሰተውን መንፈሱን ወይም “ብራህማንን” ብቻ መገንዘብ ማለት “ሳት“ ወይም ዘለዓለማዊነቱን ብቻ መረዳት ማለት ነው፡፡ የፓራማትማ ወይም በልባችን ውስጥ የሚገኘውን የአምላክ መንፈስ ማወቅ ደግሞ፣ ”ሳት” እና “ቺት” ወይም ዘለዓለማዊነቱን እና ሙሉ ፍጹም ዕውቀት ያለው መሆኑን መረዳት ማለት ነው፡፡ ነገር ግን በመንፈሳዊ ዓለም የሚገኘውን ዓብዩ የመንግሥተ-ሰማያትን ጌታ መረዳት ማለት፣ መላ መንፈሳዊ ባሕሪይውን ወይም “ሳት፣ ቺት፣ አናንዳ (የደስታ)” ባሕሪያቱን ጭምር መረዳት ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው ዓብዩ ጌታን በትክክል ሊረዳ የሚችለው እነዚህን ሦስቱን የፍጹም እውነት ባሕርዮች በተሟላ መንገድ ሲረዳ ነው፡፡ “ቪግራሀ” ማለት አካል ወይም ቅርጽ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሁለንተናው የተሟላው ዓብዩ ጌታ መንፈሳዊ አካል ወይም ቅርጽ የሌለው አይደለም። መንፈሳዊ አካል የሌለው ወይም ከፈጠረው ፍጥረታት ያነሰ ባሕርይ ያለው ከሆነማ፣ ሁለንተናው የተሟላ ዓብይ ጌታ ሊሆን አይችልም፡፡ ሁለንተናው የተሟላው ዓብዩ ጌታ በልምዳችን የምናየውን ነገር ሁሉ እና ከልማዳችን ውጪ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ አካቶ የያዘ ነው፡፡ አለበለዚያ ግን ሁለንተናው የተሟላ ነው ሊባል አይችልም፡፡

ሁለንተናው የተሟላው ዓብዩ ጌታ፣ በመጠን ሊገመት የማይችል ኅይል ያለው ነው፡፡ እነዚህም እያንዳንዳቸው ኃይላት፣ ሁለንተናቸው የተሟላ ሆነው ይገኛሉ፡፡ እንደዚህም ሁሉ ይህም ለዓይናችን የተከሰተው ቁሳዊ ዓለምም፣ በዓብዩ ጌታ የተሟላ በመሆን የተፈጠረ ነው፡፡ ይህ መላ ቁሳዊ ጠፈር የተገነባው በሃያ አራት ንጥረ ነገሮች ሲሆን፣ የጊዜ ገደብ ያለው እና ማናቸውንም ነገር ለመፍጠር፣ ለማስተዳደር እና ለመንከባከብ ሁሉን ነገር አካቶ እና አሟልቶ በዓብዩ ጌታ የተፈጠረ ነው፡፡ እነዚህንም ጠፈሮች ለመንከባከብ ማንም የሌላ ፍጥረት እጅ አያስፈልጋቸውም፡፡ ይህ መላ ቁሳዊ ጠፈር የሚተዳደረው ለራሱ በተወሰነለት የጊዜ ገደብ ነው፡፡ ይህም የጊዜ ገደብ የተወሰነው ሁለንተናው በተሟላው በዓብዩ ጌታ ነው፡፡ ይህም የጊዜ ገደብ ሲያበቃ፣ የምናየው ጊዜያዊ የጠፈር ክስተት በሙሉ ሁለመናው በተሟላው በዓብዩ ጌታ ፈቃድ የሚደመሰስበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ይበቃል፡፡

ለትናንሾቹ ሁለንተናቸው ለተሟላ ሕያው ፍጥረታት ሁሉ፣ በዚህ ዓለም ሁለንተናው የተሟላውን ዓብዩ ጌታን በትክክል ለመረዳት እንዲችሉ፣ የሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ ቀርቦላቸው ይገኛል፡፡ ስለ ሁለንተናው የተሟላው የዓብዩ ጌታ፣ ያለን ዕውቀት ያነሰ ከሆነ፣ በዓለም ላይ የተለያዩ ጉድለቶች ያሉ መስሎን ሊታየን ይችላል፡፡ ይህ በተፈጥሮ የተሰጠን የሰው ልጅ ሕይወት፣ ከሕያው ፍጥረታት መሀከል ሁሉ በከፍተኛ ንቃት የተሟላ ሆኖ ተፈጥሯል፡፡ ይህንን ዓይነት የትውልድ ዕድል ያገኘነውም፣ የ8,400,000 ዓይነቶች የተለያዩ የሕያው ፍጥረታትን ሕይወት በሂደት በተደጋገመ መንገድ በመወለድ አሳልፈናቸው ነው፡፡ ይህም ማለት በቁጥር ሊተመን የማይችል የተደጋጋሚ ትውልድ እና ሞትን ካሳለፍን በኋላ ነው፡፡ ይህንንም የሰው ልጅ ትውልድ ዕድል አግኝተን እና ከፍተኛ ንቃት ተሰጥቶን፣ ሁለመናው ከተሟላው ከዓብዩ ጌታ ጋር ያለንን ግንኙነት ለመረዳት የማንጠቀምበት ከሆነ፣ የተፈጥሮ ሕግጋትን ተከትለን እንደገና ወደ ትውልድ እና ሞት የተደጋጋሚ ኑሮ ውስጥ እንገባለን፡፡

እራሳችንንም ለመንከባከብ፣ ሁሉም ነገር በተፈጥሮ የተሟላ ሆኖ እንደቀረበለንም ስላልተረዳን፣ በተፈጥሮ የቀረበልንን ሁሉ በመበዝበዝ፣ ስሜታዊ ደስታችንን ከፍ ለማድረግ ሲባል፣ ብዙ ትግል ስናደርግ እንገኛለን፡፡ የሕያው ፍጥረታት ንቃት ሁለመናው ከተሟላው ዓብዩ ጌታ ጋር ካልተዛመደ፣ በምንም ዓይነት የስሜታዊ እና የዓለማዊ ደስታ ሊረካ አይችልም። ይህንንም ዓይነት የስሜታዊ እና የዓለማዊ የደስታ ፈለግ የምንከተለው፣ በሐሰታዊ ራእያችን ስለምንመራ ነው፡፡
እጃችን ሊረካ የሚችለው ከገላችን ጋር እስከተያያዘ ድረስ ብቻ ነው፡፡ ከገላችን ከተገነጠለ ግን ሲያዩት እጅ ይመስላል እንጂ፣ ምንም ዓይነት የእጅ ኅይል ሊኖረው አይችልም። እንደዚህም ሁሉ መላ ሕያው ፍጥረታት፣ የዓብዩ ጌታ ወገን ናቸው፡፡ ሁለንተናው ከተሟላው ከዓብዩ ጌታ ተገንጥለው ለመኖር የሚሹ ከሆነ ግን፣ ይህ የሐሰት ራእይ የሞላበት ቁሳዊ ዓለም፣ የሚፈልጉትን ደስታ ሊሰጣቸው አይችልም፡፡

የሰው ልጅ የተሟላውን ደስታ ሊያገኝ የሚችለው፣ ሁለንተናው የተሟላውን ዓብዩ ጌታን ማገልገል ሲጀምር ብቻ ነው፡፡ በዚህ ዓለም ላይ የምናቀርባቸው አገልግሎቶች ሁሉ፣ ማለትም እንደ የኅብረተሰብ፣ የፖሎቲካ፣ የማኅበረሰብ፣ የዓለም አቀፍ ወይም በፕላኔቶች መሀከል ያሉት አገልግሎቶች ሁሉ፣ ከዓብዩ ጌታ አገልግሎት ጋር የተዛመዱ ካልሆኑ፣ የተሟሉ ሊሆኑ አይችሉም። ቢሆንም ግን፣ እነዚህ ተገንጥለው የሚታዩ አገልግሎቶች ሁሉ፣ ሁለንተናው ከተሟላው ከዓብዩ ጌታ አገልግሎት ጋር የተዛመዱ ከሆኑ፣ አገልግሎቶቹ ሁሉ ስኬታማ ለመሆን ይበቃሉ፡፡

« Previous Next »