No edit permissions for Amharic

ማንትራ አስራ አምስት

ሂራንማዬና ፓትሬና
ሳትያስያፒሂታም ሙክሀም
ታት ትቫም ፑሳን አፓቭርኑ
ሳትያ ድሀርማያ ድርስታዬ

ሂራንማዬና — ወርቃማ በሚመስለው የብርሃን ግርማ ሞገስ፣ ፓትሬና — በመብለጭለጭ ለማየት የሚያታክት ሽፋን፣ ሳትያስያ — የዓብዩ ፍጹም እውነታ፣ አፒሂታም — የተሸፈነ፣ ሙክሀም — ፊቱ፣ ታት — ያ ሽፋኑ፣ ትቫም — አንተው፣ ፑሻን — ኦ የምንትከባከበን ጌታ ሆይ፣ አፓቭርኑ — በቸርነትህ አስወግደው፣ ሳትያ — ንጹሕ፣ ድሀርማያ — ለአገልጋዩ፣ ድርስታዬ — ለማሳየት።

ኦ ጌታዬ ሆይ፤ ሕያው ፍጥረታትን ሁሉ በፍቅር የምትንከባከብ፤ መንፈሳዊ ገላህ የፀሐይ ጮራን የመሰለ መንፈሳዊ ብርሃንን ስለሚያንጸባርቅ፣ ቅዱስ ፊትህን ለማየት አዳጋች ሆኗል። በመሆኑም፣ እባክህን ይህንን የመንፈሳዊ ብርሃን ጮራህን ገለል አድርገህ፣ ቅዱስ ፊትህን ለማየት እንዲችሉ፣ ለትሑት እና ለንጹሕ አገልጋዮችህ መንፈሳዊ ኃይሉን ስጣቸው፡፡

በብሀገቨድ ጊታ (ብጊ 14:27) ውስጥ እንደተገለጸው፣ ዓብዩ ጌታ ከገላው ስለሚመነጨው መንፈሳዊ የብርሃን ጮራ (ብራህማጆይቲ) እንዲሁም ስለሚያብረቀርቀው መንፈሳዊ ገላው እንዲህ በማለት ገልጾልናል።

ብራህማኖ ሂ ፕራቲሽትሀሀም
አምርታስያ ቭያያስያ ቻ
ሳስቫታስያ ቻ ድሀርማስያ
ሱክሀስያ ኢካንቲካስያ ቻ

“ከገላዬ የሚመነጨው እና ሰብአዊ ላልሆነው “የብራህማን” የብርሃን ጮራ፣ ምንጩ እኔው ነኝ። ይህም የመንፈሳዊ የብርሃን ጮራ የማይሰወር፣ የማይጠፋ እና ዘለዓለማዊ ነው። የደስታም ሁሉ መነሻ ቦታ ነው።” ብራህማን፣ ፓራፓትማ እና ብሀገቫን ተብለው የሚታወቁት ሦስቱ የመንፈሳዊ ዕውቀት ደረጃዎች፣ የዓብዩ ጌታ ፍጹም የሆኑ ሦስት መንፈሳዊ ገጽታዎቹ ናቸው። በመንፈሳዊ ብልጽግና በመጀመር ደረጃ ላይ የሚገኙት መንፈሳውያን፣ የብራህማን ገጽታውን በቀላሉ ይረዱታል። ሁለተኛው የፓራማትማ ገጽታው ደግሞ፣ ከጀማሪዎቹ ይበልጥ በመካከለኛ የመንፈሳዊ ኑሮ ለበለጸጉት፣ የደረሱበት የመንፈሳዊ ዕውቀት ደረጃ ነው። የብሀገቫን ገጽታን በትክክል የተረዱ ደግሞ፣ ከፍተኛውን መንፈሳዊ ዕውቀት የያዙ እና፣ የዓብዩ ጌታን ዓብይ ሰብአዊ አካል እና ፍጹምነት በትክክል የተረዱ ናቸው። ይህም በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ተገልጾልናል። (ብጊ 7:7) ዓብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽና እንደገለጸውም እርሱ የሦስቱም ፍጹም የሆኑት ገጽታዎቹ ዋነኛ መነሻ ነው። “ማታህ ፓራታራም ናንያት” ሽሪ ክርሽና፣ የብራህማ ጆይቲ እና የፓራማትማ መነሻ ወይም ምንጭ ነው። ከዚህም ጋር በተያያዘ መንገድ፣ በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ሽሪ ክርሽና እንዲህ በማለት ገልጾልናል። (ብጊ 10:42)

አትሀ ቫ ባሁናይቴና
ኪም ግናቴና ታቫርጁና
ቪስታብህያሀም ኢዳም ክርስናም
ኤካምሴና ስቲሂቶ ጃጋት

“ኦ አርጁና። ይኼ ሁሉ ጥልቅ የሆነ ዕውቀት ለምን አስፈለገ? እኔ ራሴ በግሌ ብቻ ይህንን መላ ጠፈር በመንፈሳዊ ገላዬ በማዳረስ እና ልክ እንደ ምሰሶ በመያዝ ሁሉን በመንከባከብ ላይ እገኛለሁ።” በዚህ ጥቅስ እንደተገለጸው፣ ዓብዩ ጌታ ፓራማትማ ተብሎ በሚታወቀው በዚህ ፍጹም በሆነው ቅንጣቢ አካሉ ብቻ፣ መላ የቁሳዊ ዓለም ጠፈርን ተስፋፍቶ በማዳረስ ሲንከባከበው ይገኛል። በተመሳሳይም በመንፈሳዊ ዓለም ያሉትንም ሁሉ፣ ሙሉ በሙሉ በመንከባከብ ላይ ይገኛል። በዚህም ምክንያት “ሽሩቲ ማንትራ” በተባለው የሽሪ ኡፓኒሻድ መጽሐፍ ውስጥ እንደተገለጸው ዓብዩ ጌታ “ፑሳን” ወይም የበላይ ተንከባካቢ ተብሎ ይታወቃል።

ዓብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽና ሁልጊዜ ደስታ የተሞላበት ነው። “አናንዳ ማዮ ብህያሳት”። ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት ሽሪ ክርሽና በቭርንዳቫን ከተማ በህንድ አገር ውስጥ በነበረበት ጊዜ፣ ደስታ የተሞላበት ጊዜን ያሳልፍ ነበር። ይህም ገና ወደ ምድር በመጣበት ከልጅነቱ ጊዜ ጀምሮ ነው። በልጅነቱ በጊዜው የነበሩትን እንደ አግሃ፣ ባካ፣ ፑታና እና ፕራላምብሀ የመሳሰሉትን ታላላቅ እና ኅያል አጋንንትን ሲገድላቸው እንኳን፣ ልክ እንደ የደስታ ስፖርት እንቅስቃሴ አድርጎ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡
በልጅነቱ በነበረበት ሰፈርም ከእናቱ፣ ከወንድሙ እና ከጓደኞቹ ጋር በቭርንዳቫን ውስጥ በጣም ደስ የሚያሰኝ ጊዜ አሳልፎ ነበር፡፡ በልጅነቱ ለጋ ቅቤ የመስረቅ ጨዋታ ላይ በነበረበት ጊዜም፣ መላ ጓደኞቹ እና ሰፈረተኛው ሁሉ፣ ለጋ ቅቤ በመስረቁ ከፍተኛ ደስታ ይሰማቸው ነበር። በዚህም ምክንያት የለጋ ቅቤ ሌባ ተብሎ ይታወቅ ነበር። በዚህ ዓይነት ቀጣፊ በመሰለ ሥራው ግን፣ መላ ትሑት አገልጋዮቹን በደስታ ይመስጣቸው ነበር። በቭርንዳቫና ከተማ ውስጥ ያደረገው ነገር በሙሉ፣ ለትሑት አገልጋዮቹ ከፍተኛ ደስታን የሚሰጥ ነበር። ዓብዩ ጌታም ይህንን ታሪክ የሚፈጥረው፣ መንፈሳዊ እና ግምታዊ ፈላስፎችን እና “በሀትሀ ዮጋ” የተመሰጡትን ሁሉ ፍጹም ወደ ሆነው ወደ ዓብይ ሰብአዊው ጌታ እንዲያተኩሩ ለመሳብ ነው።

ዓብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽና በምድር ላይ በነበረበት ወቅት፣ ስለ ልጅነት ጊዜው እና ከጓደኞቹ ጋር የነበረውን ሕይወት፣ መምህሩ ሹካዴቫ ጎስዋሚ ሲገልፅልን፣ እንዲህ በማለት አስረድቶናል። (ሽብ 10.12.11)

ኢትሀም ሳታም ብራህማ ሱክሀኑ ብሁትያ
ዳስያም ጋታናም ፓራ ዳይቫቴና
ማያስሪታናም ናራ ዳራኬና
ሳካም ቪጃህሩህ ክርታ ፑንያ ፑንጃህ

“ዓብዩ የመንግሥተ-ሰማያት ጌታ፣ “በግያኒዎች” የሚታወቀው ሰብአዊ ገላ እንደሌለው በመቆጠር ሲሆን፣ የያዙትም እምነት፣ ዓብዩ ጌታ ልክ እንደ ደስተኛ “የብራህማን” ጮራ ነው በማለት ነው። በትሑት አገልጋዮቹ ግን፣ እንደ ዓብይ ሰብአዊ ጌትነቱ፣ በቤተ መቅደስ ውስጥ መንፈሳዊ አካሉ ተመስሎ ሲሰገድለት ይገኛል። ወደ ምድር በወረደም ጊዜ በመንፈሳዊ ዕውቀት ባልዳበሩ ተራ የሰው ልጅ አስተሳሰብ ባላቸው ሰዎች ዘንድ ደግሞ ልክ እንደ ገነነ ተራ የሰው ልጅ ሆኖ ይታይ ነበር። “ዓብዩ የመንግሥተ-ሰማያት ጌታ፣ “በግያኒዎች” የሚታወቀው ሰብአዊ ገላ እንደሌለው በመቆጠር ሲሆን፣ የያዙትም እምነት፣ ዓብዩ ጌታ ልክ እንደ ደስተኛ “የብራህማን” ጮራ ነው በማለት ነው። በትሑት አገልጋዮቹ ግን፣ እንደ ዓብይ ሰብአዊ ጌትነቱ፣ በቤተ መቅደስ ውስጥ መንፈሳዊ አካሉ ተመስሎ ሲሰገድለት ይገኛል። ወደ ምድር በወረደም ጊዜ በመንፈሳዊ ዕውቀት ባልዳበሩ ተራ የሰው ልጅ አስተሳሰብ ባላቸው ሰዎች ዘንድ ደግሞ ልክ እንደ ገነነ ተራ የሰው ልጅ ሆኖ ይታይ ነበር።

ዓብዩ ጌታ ከትሑት አገልጋዮቹ ጋር ፍቅር በተሞላበት የመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ሁልጊዜ በመሳተፍ ላይ ይገኛል። እነዚህም ግንኙነቶች በአምስት ይከፈላሉ። “ሳንታ” ገለልተኛነት፣ “ዳስያ” አገልጋይነት፣ “ሳክያ” ጓደኝነት፣ “ቫትሳልያ” ወላጅነት፣ “ማድሁርያ” ፍቅረኝነት።

ዓብዩ ሽሪ ክርሽና በመንፈሳዊው ዓለም የሚገኝበትን፣ የመኖሪያውን “ቭርንዳቨን ድሀምን” ቦታ አይለቅም ተብሎ በቬዲክ መጻህፍት ውስጥ ተገልጿል። አንድ ሰው ግን “ታድያ እንዴት አድረጎ ነው የዚህን ዓለም ጉዳዮች ሊያስተዳድር የሚችለው?” ብሎ ይጠይቅ ይሆናል። ይህም በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ተገጾልናል። (ብጊ 13: 14-18) “ዓብዩ ጌታ በመላው የቁሳዊው ጠፈር ውስጥ “ፓራማትማ” ወይም “ዓብዩ ነፍስ” ተብሎ በሚታወቀው በከፊል ወገኑ በመስፋፋት መላ ቁሳዊ ዓለምን በማዳረስ ሲያስተዳድር ይገኛል። ምንም እንኳን ዓብዩ ጌታ በቁሳዊው ዓለም የመፈጠር፣ የመንከባከብ እና የመደምሰስ ሥራ ላይ በቀጥታ የማይሳተፍ ቢሆንም፣ “ፓራማትማ” ተብሎ በሚታወቀው ከፊል ወገኑ ግን፣ የእነዚህ ሁሉ እንቅስቃሴዎች ምንጭ እና መሠረት ሆኖ ይገኛል። እያንዳንዱ ሕያው ፍጥረታት “አትማ” ወይም ነፍስ ተብለው ይታወቃሉ። እነዚህንም ሕያው ፍጥረታት ሁሉ በበላይነት የሚቆጣጠረው ደግሞ “ዓብዩ ነፍስ” ወይም በሳንስክሪት ቋንቋ “ፓራም አትማ” ተብሎ ይሚታወቀው የዓብዩ ጌታ አካል ነው።

ይህ ነፍስን እና ዓብዩ ጌታን በትክክል የመረዳት ትምህርት እና ሥርዓት ታላቁ ሳይንስ ነው። “ሳንክያ ዮጊዎች” ተብለው የሚታወቁት ዓለማዊ ፈላስፎች፤ ትኩረት የሚያደርጉት ሁሉ፣ ዓብዩ ጌታ በፈጠራቸው በሀያ አራቱ የቁሳዊው ዓለም ፍጥረታት ንጥረ ነገሮች ላይ ነው። በዚህም ምክንያት ስለ ዓብዩ ጌታ ወይም “ፑሩሻ” በጣም የተወሰነ ዕውቀት ብቻ ነው ያላቸው። በዓብዩ ጌታ የሰብአዊ ገላ የማያምኑ መንፈሳውያን ደግሞ በዓብዩ ጌታ መንፈሳዊ የብርሃን ጮራ ወይም “ብራህማ ጅዮቲ” ኅይል ብቻ የሚደነቁ ናቸው። አንድ ሰው ዓብዩ ጌታን በትክክል ለመረዳት ግን ከሀያ አራቱ የቁሳዊ ዓለም ንጥረ ነገሮች እና፣ ከመንፈሳዊው የዓብዩ ጌታ ብርሃን ጮራ (ብራህማጆይቲ) ባሻገር፣ ዓብዩ ጌታን መረዳት ያስፈልገዋል። በዚህ ጥቅስ ላይ እንደተጠቀሰውም ሽሪ ኡፓኒሻድም የሚያስተምረን ይህንኑ ነው። ይህም የዓብዩን ጌታ “ሂራንማያ ፓትራ” ወይም የሚያጸባርቅ እና የሚያምር ኃይሉን ገለል በማድረግ እርሱ ራሱን በትክክል እንድንረዳው በመጸለይ ነው። ይህ የሚያንጸባርቅ የመንፈሳዊ ብርሃን ጮራው እና ለእርሱ ያለው አድናቆት ገለል ካላለ፣ አስደናቂው እና መንፈሳዊ ሰባዓዊ ገላውን ፊት ለፊት በማየት ለመቅረብ አዳጋች ይሆናል። በዚህ ምክንያት ይህ ለብርህማጆይቲ ያለን አድናቆት ብቻ ፍጹም የሆነውን የዓብዩ ጌታን ሰባዓዊ መንፈሳዊ አካል በትክክል ለመመመልከት እና ለመረዳት እንዲሳነን ያደርገናል።

“ፓራማትማ” ተብሎ የሚታወቀው የዓብዩ ጌታ ከፊል ወገን ደግሞ፣ “ቪሽኑ ታትቫ” ተብሎ ከሚታወቀው ከሦስቱ የዓብዩ ጌታ የቪሽኑ አካል ከፊል ወገኖች አንዱ ነው። እነዚህ ሦስቱ የዓብዩ ጌታ የቪሽኑ ከፊል ወገኖች “ፑሩሻ አቫታር” ይባላሉ። ከእነዚህም የቪሽኑ ታትቫ ሦስቱ ወገኖች፣ በዚህ የቁሳዊ ዓለም ጠፈር ውስጥ የሚኖረው አንዱ “ክሺሮዳክሻዪ ቪሽኑ” ይባላል። ይህም ቪሽኑ ብራህማ፣ ቪሽኑ፣ ማሄሽ ተብለው ከሚታወቁት ከሦስቱ መላእክት አንዱ ነው። ፓራማትማ ወይም ዓብይ ነፍስ እንደመሆኑም፣ በመላው ቁሳዊ ዓለም ውስጥ እና በእያንዳንዱ የሕያው ፍጥረታት ልብ ውስጥ ተሰራጭቶ ይገኛል። በዚህ ቁሳዊ ዓለም ውስጥ የሚገኘው ሁለተኛው የቪሽኑ ታትቫ መንፈሳዊ አካል ደግሞ፣ “ጋርቦዳክሻዪ ቪሽኑ” ነው። እርሱም በመላ ቁሳዊ ጠፈር ውስጥ ለሚገኙት ሕያው ፍጥረታት ሁሉ፣ የበላይ አስደዳዳሪ ዓብይ ነፍስ ነው። ከእነዚህ ከሁለቱ የዓብዩ ጌታ ከፊል ወገኖች ባሻገር፣ “ካራኖ ዳክሻዪ ቪሽኑ” ተብሎ የሚታወቀው ዓብዩ ቪሽኑ ይገኛል። እርሱም ከቁሳዊ ዓለም ባሻገር በሚገኘው፣ “ካራን ውቅያኖስ” ላይ ይገኛል። ይህም የቪሽኑ አካል መላ ቁሳዊ ዓለምን የፈጠረ የዓብዩ ጌታ አካል ነው። የዮጋ ትምህርትም የሚያስተምረን ከእነዚህ ሀያ አራት የቁሳዊ ዓለም ንጥረ ነገሮች ባሻገር በመሄድ፣ እንዴት እነዚህን ሦስቱን ቪሽኑ ታትቫን መረዳት እንደምንችል ነው። ይህም ዕውቀት በምርምር ላይ የተመሠረተ የፍልስፍና ባህል እና፣ የዓብዩ ጌታን “ብራህማ ጅዮቲ”፣ ወይም ከዓብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽና የሚመነጨውን የመንፈሳዊ ብርሃን ጮራን በትክክል እንድንረዳው ይደግፈናል። ስለዚህም በሚመለከት የሽሪ ክርሽና የመንፈሳዊ ብርሃን ጮራ በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ (ብጊ፡ 14:27) እና በብራህማ ሰሚታ (ብሰ፡ 5:40) ውስጥ ተገልጾልናል።

ያስያ ፕራብሀ ፕራብሀቫቶ ጃጋድ አንዳ ኮቲ
ኮቲስቭ አሼሻ ቫሱድሀዲ ቪብሁቲ ብሂናም
ታድ ብራህማ ኒስካላም አናንታም አሼሻ ብሁታም
ጎቪንዳም አዲ ፑሩሻም ታም አሀም ብሃጃሚ

“በሚሊዮን በሚቆጠሩት በእያንዳንዱ የቁሳዊ ዓለም ጠፈር ውስጥ፣ በቁጥር ሊተመኑ የማይችሉ ፕላኔቶች ይገኛሉ። እነዚህም እያንዳንዳቸው በቁሳዊ አፈጣጠር የተለያዩ ናቸው። የሚገኙትም ብራህማ ጅዮቲ በተባለው የዓብዩ ጌታ መንፈሳዊ ጮራ ጥግ ላይ ነው። ይህም ብራህማ ጅዮቲ የሚባለው፣ የዓብዩ ጌታ “ጎቪንዳ” መንፈሳዊ የብርሃን ጮራ ነው። የሚመነጨውም ከምሰግድለት የዓብዩ ጌታ ጎቪንዳ መንፈሳዊ ገላ ነው።” ይህ ጥቅስ የተመዘገበው “በብራህማ ሰሚታ” ውስጥ ነው። የተነገረውም ስለ ዓብዩ ጌታ ፍጹምነት በትክክል በተገነዘበው በጌታ ብራህማ ነው። “ሽሩቲ ማንትራ” ተብሎ የታወቀው የሽሪ ኡፓኒሻድ ትምህርትም የዚህን ጥቅስ መልእክት፣ ዓብዩ ጌታን ለመረዳት የሚያስችል አገላለጽ እንዳለው ገልጾታል። በዚህ የኢሾፓኒሻድ ማንትራ ወይም ጥቅስ ውስጥ የሚያካትተው ጸሎት፣ የዓብዩ ጌታን ትክክለኛ መንፈሳዊ ገላ እና ፊቱን ለመመልከት እንድንችል ለብርሃን ጮራው ያለንን አድናቆት ገለል እንዲጋርድልን ነው። ስለዚህም የብራህማ ጆይቲ ይብርሃን ጮራ “በሙኩንዳ ኡፓኒሻድ” ውስጥ በተለያዩ ጥቅሶች ተገልጾልናል። (ሙኡ፡ 2:2፡ 10 – 12)

ሂራንማዬ ፓሬ ኮሴ
ቪራጃም ብራህማ ኒስካላም
ታክ ቹብህራም ጅዮቲሳም ጅዮቲስ
ታድ ያድ አትማ ቪዶ ቪዱህ

ና ታትራ ሱርዮ ብሀቲ ና ቻንድራ ታራካም
ኒማ ቪድዩቶ ብሀንቲ ኩቶ ያም አግኒህ
ታም ኤቫ ብሀንታም አኑ ብሀቲ ሳርቫም
ታስያ ብሃሳ ሳርቫም ኢዳም ቪብሃቲ

ብራህማኢቬዳም አምርታም ፑራስታድ ብራህማ
ፓስቻድ ብራህማ ዳክሲናታስ ቾታሬና
አድሀስ ኮርድህቫም ቻ ፕራስርታም ብራህማይ
ቬዳም ቪስቫም ኢዳም ቫሪስትሃም

“ከዚህ ቁሳዊ ዓለም ባሻገር እና መንፈሳዊው ዓለም በሚገኝበት ውስጥ፣ የብራህማን መንፈሳዊ ጮራ ይገኛል። ይህ መንፈሳዊ የብርሃን ጮራ በዓለማዊ መንፈስ የተበከለ አይደለም። በመንፈሳውያን እንደሚታወቀው ይህ የጸዳ ነጭ ብርሃን፣ የብርሀናት ሁሉ ዋና የብርሃን ምንጭ ነው። በዚህ መንፈሳዊ ዓለም ውስጥ የፀሐይ፣ የጨረቃ፣ የእሳት ወይም የኤሌክትሪክ ብርሃን አያስፈልግም። በዚህ በቁሳዊ ዓለም የሚገኘው የተፈጥሮ ጮራ ሁሉ፣ የዚሁ የመንፈሳዊው ጮራ ቅንጣቢ ነጸብራቅ ነው። ይህም ብራህማን ተብሎ የሚታወቀው ጮራ በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ በፊትም፣ በኋላም፣ በሰሜን፣ በደቡብ፣ በምሥራቅ እና በምዕራብ እንዲሁም በላይ እና በታች የሚገኝ ነው። በአጠቃላይ ይህ የብራህማን ጮራ፣ መላ የመንፈሳዊ እና የቁሳዊ ዓለማትን የሚያዳርስ ነው።”

ትክክለኛ ዕውቀት ማለትም ሽሪ ክርሽና የዚህ የብራህማን መንፈሳዊ ነጸብራቅ ዋነኛ ምንጭ መሆኑን መረዳት ማለት ነው። ይህ ዕውቀት ሽሪማድ ብሀገቨታምን ከመሳሰሉ መጻሕፍት ውስጥ በሰፊው ተገልጾ ይገኛል። እነዚህ መጻሕፍቶች ስለ ሽሪ ክርሽና ሳይንሳዊ ዕውቀት በጥልቅ የሚያስተምሩ ናቸው። በሽሪማድ ብሀገቨታም ውስጥ ደራሲው ሽሪላ ቭያሳዴቭ እንደገለጸው፣ አንድ ሰው ስለ ብራህማን፣ ፓራማትማ እና ብሀገቫንን በትክክል ሊረዳ የሚችለው፣ ከያዘው ከመንፈሳዊ ዕውቀት ብቃት እና አኳያ ነው። ሽሪላ ብቫያሳዴቭ እንደገለጸው፣ ጂቫ ወይም ተራው ነፍስ ፈጽሞ እንደ ዓብዩ ጌታ ሊሆን ይችላል በማለት አይገልጽም። ሕያው ፍጥረታት ልክ እንደ ኃያሉ ዓብይ ጌታ ለመሆን ወይም ፈጽሞ ሊወዳደሩ አይችሉም። እንደ ዓብዩ ጌታ ኅያል ቢሆኑማ የብርሃን ጮራውን እንዲያስወግድላቸው እና መንፈሳዊ ገላውን እና ፊቱን እንኳን ለመመልከት እንዲችሉ አይጸልዩም ነበር።

ይህን መልእክት ማጠቃለል የሚቻለው፣ አንድ ሰው ስለ ዓብዩ ጌታ ኅያልነት ትክክለኛ ዕውቀት ከሌለው፣ ምንም ያህል ቢመራመር በከፍተኛነት ሊገነዘብ የሚችለው ሰብአዊ ያልሆነውን ብራህማን ወይም መንፈሳዊ ጮራውን ብቻ ነው። እንደዚሁም ሁሉ አንድ ሰው ስለ ዓብዩ ጌታ የቁሳዊ ዓለም ኃይላት በትክክል የሚረዳ ከሆነ እና፣ ስለ መንፈሳዊው የዓብዩ ጌታ ኃይላት ትንሽ ወይም የተወሰነ ዕውቀት ካለው ሊገነዘብ የሚችለው “የፓራም አትማ”ን ከፊል ወገኑን ብቻ ነው። ስለዚህ እነዚህ ሁለቱ የዓብዩ ጌታ “የብራህማን” እና “የፓራማትማ” ግንዛቤዎች ከፊል ግንዛቤዎች ናቸው ማለት ነው። ነገር ግን ከዚህ ባሻገር የመንፈሳዊ ጮራው “ሂራንያ ጋርባ” የተወገደለት ሰው፣ ዓብዩ የመንግሥተ-ሰማያት ጌታ ሽሪ ክርሽናን በትክክል የተረዳ ሰው ነው። ይህም “ቫሱዴቫ ሳርቫም ኢቲ” ይባላል። ዓብዩ ሽሪ ክርሽና “ቫሱዴቭ” ይባላል። እርሱም ሁሉንም ወገኖች ያካተተ ነው። እነዚህም ብራህማን፣ ፓራማትማ እና ብሀገቫንን ናቸው። ሽሪ ክርሽና “ብሀገቫን” በመባል ይታወቃል። የእነዚህ የከፊል ወገኖቹ ሁሉ ምንጭ ወይም ሥር ብሀገቫን ነው። ብራህማን እና ፓራማትማ ተብለው የሚታወቁት ከፊል ወገኖቹ ደግሞ፣ ልክ እንደ ቅርንጫፎቹ በመሆን ይታወቃሉ።

በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ (ብጊ 6፡ 46-47) እነዚህን ሦስቱን ዓይነት መንፈሳውያን የሚያወዳድር ገለጻ ቀርቦልናል። እነዚህም ሦስቱ “ግያኒ” ተብለው የሚታወቁት ሰብአዊ ያልሆነውን ብራህማን የሚያመልኩት ሲሆኑ፣ “ዮጊ” ተብለው የሚታወቁት ደግሞ “ፓራም አትማ”ን የሚያመልኩ ናቸው። “ብሀክታ” የተባሉት ደግሞ፣ የዓብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽና “ብሀገቫን” አገልጋዮች ናቸው። እዚህም እንደተገለጸው “ግያኒ” እና የቬዲክ ዕውቀትን የተከታተሉ ሰዎች፣ ለጥቅሙ ከቆመ ከሰፊው ሕዝብ ጋር ሲወዳደሩ፣ የተሻሉ ናቸው። ዮጊዎች ደግሞ ከግያኒዎች የተሻሉ ሆነው ይገኛሉ። ከመላ ዮጊዎች መሀከል ግን ዓብዩ ጌታን በትሑት መንፈስ እና በፍቅር የሚያገለግሉ ሁሉ “ብሀክታዎች” የበላይ ናቸው። በአጭሩ ለማጠቃለልም ፈላስፋዎቹ ከተራ የቀን ሠራተኛው የተሻሉ ናቸው። ምስጢራዊ ኅይል ያላቸው ዮጊዎች ደግሞ ከፈላስፋዎቹ ይሻላሉ። ከእነዚህ ሁሉ ዮጊዎች መሀከል ግን “ብሀክቲ ዮጋን” የሚከተሉት የዓብዩ ጌታ ትሑት አገልጋዮች፣ በከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ናቸው። የዚህ የሽሪ ኡፓኒሻድ ትምህርትም የሚያበረታታን፣ ወደ እዚህ ደረጃ እና የመንፈሳዊ በላይነት ብቃት ላይ እንድንደርስ ነው።

« Previous Next »